ለጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላ የተፈቀደው ዋስትና ተከለከለ

በአንዋር መስጊድና አካባቢው ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በተፈጠረ ግጭትና ሁከት ተሳትፈዋል በሚል ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው ከሚገኙ 14 ተጠርጣሪዎች መካከል ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ለሦስት ሰዎች ፍርድ ቤት ትናንት ጠዋት ፈቅዶት የነበረው የ5 ሺህ ብር የዋስትና መብት ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በቀረበ ይግባኝ ውድቅ ሆኖ ዋስትናው ተከለከለ።
ሜክስኮ በሚገኘው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዮች የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት የዛሬ ሳምንት የተሰጣቸውን የጊዜ ቀጠሮ ተከትሎ በችሎት ካቀረቡት 14 ተጠርጣሪዎች መካከል የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛዋ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችውን ወ/ት ወይንሸት ሞላን ጨምሮ አራት የፖሊስ አባላት (ማለትም አንድ ኢንስፔክተር፣ አንድ ምክትል ኢንስፔክተርና አንድ ምክትል ሳጅንና አንድ የኮንስታብል ማዕረግ ያላቸው) እና ሌሎች ስምንት ተጠርጣሪዎች በችሎች ሲያቀርብ የተቀሩት ከሁለተኛው የጊዜ ቀጠሮ በኋላ ፖሊስ ምርመራዬን ጨርሼባቸዋለሁ ሲል ማሰናበቱን ለፍርድ ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።
አሁን ድረስ በምርመራ ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎች ጠበቃ ያልቆመላቸው ሲሆን፤ በትናንት ጠዋቱ የችሎት ውሏቸውም በባለፈው የጊዜ ቀጠሮ ወቅት ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄያቸው መሠረት ፍርድ ቤቱ፤ አዚዛ መሐመድ፣ ወይንሸት ሞላ እና ኡዝታዝ መንሱር የ5 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲሄዱ ትዕዛዝ ቢሰጥም፤ በቀደመው ችሎት ያቀረባቸውንና ምላሽ ያላቀረበባቸውን የዋስትና መቃወሚያዎች ፖሊስ ለችሎቱ አቅርቦ አስረድቷል። ይኸውም ምርመራዬን አልጨረስኩምና ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም፤ በሕክምና ላይ ያሉና ጉዳት የደረሰባቸውን የፖሊስ አባላትንም መጨረሻ ማወቅ ያስፈልጋል በሚል ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ይግባኝ መሠረት ችሎቱ ጠዋት ላይ የተፈቀደ ዋስትና በከሰዓት ላይ ውድቅ ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማረፊያ እንዲመለሱ ተደርጓል።
የምርመራ ተግባራቶቼን አላገባደድኩም ሲል ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮን የጠየቀው ፖሊስ በጥቁር አንበሳ እና በፖሊስ ሆስፒታል የሚገኙትንና በብጥብጡ ወቅት ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉትን ሰዎች ሁኔታና ቃል ተቀብሎ ለማቅረብ ፍርድ ቤቱን በጠየቀው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ የተፈቀደለት ሲሆን፤ ለመጪው ነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

Advertisements
Posted in politics | Leave a comment

ስበር ዜና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ህክምና ላይ የሚገኙት የአቶ በረከት ስሞኦን የጤነት ሁኔታ እያነጋገር ነው።

እሁድ ከአዲስ አበባ አንድ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ዶ/ር አስከትለው በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን እኩለለሊት ጅዳ ስውዲ አረቢያ ለህክምና በሚስጠር እደገቡ የሚነገርላቸው አቶ በረከት ስሞኦን በተለምዶ ብግሻን እይተባለ የሚጠራ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልቡ ደም ቧንቧ ለማስፋት የተደረገላቸው መሆኑን ከሳውዲ አየር መንገድ ምንጮቻችን ለማረጋገጥ ተችሏል ። የመንግስት ባለስልጣኑ ጤንነት በአሁኑ ሰዓት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት እንዚህ ምንጮች ዛሬ ጠዋት ከመካ የዒድ አል ፈጠር የፀሎት ስረአት ባሃላ ሼክ አላሙዲን በስልክ እንዳነጋገሯቸው ይናገራሉ። አቶ በረከት ስመኦን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ በድብቅ መምጣታቸውን የሚናገሩ እንዚህ የሳውዲ የአየር መገድ ምሲጥራዊ መረጃዎች ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ጅዳ ሆስፒታል መተኛታቸው በተለያዩ የዜና ማስራጫዎች በመዛመቱ ህክምናቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ሳይጨርሱ ወደ ሃገር ሊመለሱ እንድሚቸል ገልጸዋል።
እስካሁን የመንግስት መገኛኛ ብዙሃን በኚህ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ዙሪያ ምንም ያሉት ነገር አለመኖሩን የሚናገሩ አንዳንድ ወገኖች የአቶ በረከት ስሞን ተደብቆ እንድተራ ሰው ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ሆስፒታል ለህክምና መግባት ምናልባተም ለደህንነታቸው ሲባል የተወስደ እርምጃ ሳይሆን እንደማይቀር ይገምታሉ። ጅዳ ብግሻን ሪፈራል ሆስፒታል 4 ፎቅ ከበሽታቸው በማገገም ላይ እንደሚገኙ የሚነገረው አቶ በረከት ፍጹም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች የባለስልጣኑ የደም ግፊት አለመስተካከል በልባቸው ላይ የሚያሳድረው ተጸኖ ወደፊት ለከፍተኛ የጤና መታወክ ሊዳርጋቸው እንደሚቸል ገልጸዋል ።
በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን ተደብቀው ለህክምና ትላንት ለሊት ሳውዲ ጃዳ ስለገቡት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አቶ በረከት ስሞኦን በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ሆነ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ምንም የሚያቁት ነገር እንደሌለ ለማረጋጋጥ ተችሏል። አቶ በረከት አንድ ሴት ልጃቸውን እና ሚስታቸውን አስከትለው መምጣቸውን የሚናገሩ የአየር መንገዱ ምንጮቻችን ባለስልጣኑ በተረጋጋ ህክምና ላይ አለመሆናቸውን በተጨባጭ ማረጋገጥ ተችሏል ። ይህ በዚህ እንዳለ በአሁን ሠዓት መካ ፀሎት ላይ የሚገኙት ሼክ አላሙዲን ማምሻውን እኚህን የመንግስት ባለስልጣን ይጓበኞቻዋል ተብሎ ይጠበቃል። በአቶ በረከት ዙሪያ የሚደርሱንን አዳዲስ ተጨማሪ መረጃዎች እይተከታተለን የምናቀርብ መሆኑንን እናስታውቃለን ።

Posted in politics | Leave a comment

ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀውን የዜጎች ቃል-ኪዳን ሰነድ (ሕገ መሰረት) ለህዝብ ይፋ አደረገ

የዜጎች ቃል-ኪዳን ሰነድ ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ

ክፍል ፩
መግቢያ
ይህ የዜግነት ቻርተር (ቃል-ኪዳን እና ሕገ-መሠረት) ከፖለቲካዊ አድናቂነት ነጻ የሆነ፤ ሁሉን-አቀፍ ምሰሶ የሆኑ መርህዎችን ያካተተ የማሕበረሰብ (የሲቪክ) ንቅናቄ ሰነድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከየት ወደ የት ለሚለው አንገብጋቢ ጥያቄም መሰረታዊ መልስን ያቀፈ ራዕይን የሚያስተጋባ የኩሩ ዜጎች መለያ ነው፡፡ ይህም ማለት፡-
• ቃልኪዳኑ ግልጽና ሁሉን-አቀፍ ሕብረተሰብ ለመገንባት የሚጠቅሙ የሲቪክ ባህሎችን ለማዳበር፤
• በዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት፤ ሉዓላዊነት፤ ማህበረሰባዊ የራስ-በራስ አስተዳደርን የመሳሰሉ ልምዶች እንዲሰፍኑ በጠቅላላው መልካም የስልጣን አጠቃቀም ስነ-ምግባርን እውን ለማድረግ ለተነሳሱ ዜጎች፣ የሲቪክ ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድነትና የወል ራእይና መመሪያ ሆኖ እንዲያገለግል፤
• በዓለም-አቀፍ ተቀባይነት ያገኙ የሰብአዊ፣ የሲቪል፣ የባህልና የፖለቲካ ሁለንተናዊ መብቶች በመንግሥት ብቻ ሳይሆን ነገ ለልጆቻችን የምናወርሰውን በጎና መልካም ነገር ሁሉ በሚያስብ መንፈስ በዜጎችም እንዲጠበቁ የሚያስችል የሲቪክና የፖለቲካ ጥምር እንቅስቃሴን እውን ለማድረግ አስፈላጊነቱን ለማስገንዘብ፤
• የረጅም ጉዞ እንቅስቃሴውን ፍሬያማ ለማድረግ ደግሞ ለግለሰብ ነጻነትና ክብር መጠንቀቅ፣ የህብረተሰብን ጥቅም ማቀፍ፣ የተለያዩ ባህሎችን ማክበር እና አዎንታዊ አመለካከት እንዲዳብር በማድረግ መሠረታዊ እሴቶችን መደገፍ ዋና ተግባሩ ነው፡፡

ስለሆነም የዛሬው ትውልድ የነገይቱን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚገነባባቸው የኢትዮጵያዊነት መንፈስና የስልጣኔያችን መለዮች መሆናቸውን አጉልቶ ለማሳየት፤
• አበው ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እንዳሉት፤ የሲቪክ ማህበራትን ንቃትና በአንድ ግንባር ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የምንሻው ህዝባችንን ከአገዛዝ ስርአት እና ከጨቋኝ መንግስታዊ ስርዓት ለማውጣት ብቻ ሳይሆን ተመልሶም ለጭቆና እና ለአገዛዝ እጅ ላለመስጠትና ላለመንበርከክ መብቱን እና ሰብአዊ ክብሩን አስጠብቆ ከማንም ሳይለምን በፍቅር ተደራጅቶ ለመቆም ዋስትና የመሆን ሚና ስላለው ነው፡፡ ይህም በመሆኑ መብትና ግዴታዎችን በጽኑ እውን ለማድረግ የሚካሄደውን ትግል ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲደግፉ ጥሪውን ለማስተጋባት፣ በመጨረሻም
• ኢትዮጵያውያን በነፃነት መብትና ግዴታችንን በማክበር በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ አዲስ የአስተዳደር ባህል እንድናዳብር እና ይህ መልካም አስተሳብ ተግባራዊ መሆን ያለበት ወቅትም በመሆኑ ይህ ሰነድ አስፈላጊነቱ እጅግ የጎላ ነው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ የምንዘረጋው ሥርዓት ሃቀኝነትንና ዜጎችን ሉዓላዊ ያደረገ፣ የምንመርጣቸው መሪዎችም ለሕዝብ አገልግሎትና ተጠያቂነት የገቡትን ቃል በመወጣትና ባለመወጣት የሚመዘኑ እንዲሆኑ ስለምንመኝ ነው፡፡
ይህ የቃል-ኪዳን ሰነድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጠንካራ የጋራ እንቅስቃሴ አድርገው ለእኩልነትና ለፍትህ የቆመ መንግስት በመመስረት ሀገራዊ ሉአላዊነትን፤ ሰብአዊ ክብርን እና የዜጎች ነፃነትን እንዲያስከብሩ የተዘጋጀ ሕገ-መሠረት ነው፡፡ በመሆኑም የሕዝብ ተጠሪ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ይህንን ሕገ-መሠረት አይተው እንዲወያዩበት፤ እንዲተቹበት እና የማሻሻያ ሀሳብ በማቅረብ ሰነዱ ውስጥ የተዘረዘሩትን መርሆዎችና አላማዎች በድርጅታዊ ፕሮግራሞቻቸው ውስጥ እንዲያካትቱ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
ክፍል ፪
ኢትዮጵያ ከየት ወደ የት?
እያንዳንዱ ትውልድ ከአባቶቹና ከእናቶቹ የወረሳቸውን መልካም የሆኑ ነገሮች ሁሉ የመጠበቅና ከዘመኑ አስተሳሰብ ጋር አስታርቆ የማቅረብ እንዲሁም ኢትዮጵያን የመጠበቅና የማስከበር ኃላፊነት አለበት፡፡ ዘመናዊዋ ኢትዮጵያም ሁሉም ዜጎቿ በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በእኩል ተሳትፎ የሚያደርጉባት የተሰፋ ምድር መሆን እንዳለባት አያከራክርም፡፡
የአሁኑን ትውልድ ምኞትና ተስፋ አዎንታዊ ለማድረግና ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ያለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ በመገንዘብ፣ ከአመለካከት አንፃር የጋራ ስምምነት እንዲኖርና ወጣቱ ትውልድ የአባቶቹን ታሪክ በውል ተረድቶ የውደፊት ምኞቱን እና ተስፋውን መንደፍ አንገብጋቢ ተግባራችን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስርዓት በቀላሉ የማይካዱ የውርስ ገጽታዎች ስላሉት ለተነሳንበት ዓላማ የሚጠቅሙትን ለምሳሌ ያህል እንጠቁማቸው፡-
• ባለፉት ብዙ ምዕተ-ዓመታት አንዴ ሲጠብ አንዴ ደግሞ ሲሰፋ በኖረው የኢትዮጵያ ግዛት ጎልተው የሚታወቁ በአንድ ጎሳ ወይም ነገድ ስም ብቻ ወይንም ክልላዊነት የተመሰረቱ ሉዓላዊ መንግስታት አልነበሩም፡፡ እርግጥ የተለያዩ መንግስታት በየዘመኑ ሃይልና ጉልበትን መሰረት ባደረገ አካሄድ የስልጣን መደላድላቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንደአንድ አገር ህዝብ ደስታና ሃዘኑን በጋራ እየተካፈለ አብዛኛውን ጊዜ ተዛምዶና በባህል ተወራርሶ ኖሯል፡፡ ይህ የተዋረሰ ባህል እርስ-በርስ እየተቆራኘ ለቀሪው ትውልድ ያቆየው ባህል ዘመናዊ ዲሞክራሲን ለመገንባት ምቹ መንደርደሪያ መሆኑ አያከራክርም፤
• በሀገሪቱ ውስጥ ክርስትና፣ እስልምናና ባህላዊ የሃይማኖት ሥርዓቶች ተፈቃቅደውና ተከባብረው መኖራቸው የአንጋፋዋ ኢትዮጵያን አብነት ያሳያል፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች ሀገር በመሆኗ፣ ተባብረው የሚኖሩበትንና የአናሳዎቹን መብት ለማስከበር የሚያስችል ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ አስፈላጊነቱ ግልጽ ነው፤
• አልፎ አልፎ ከታዩት ከባድ የፈተና ዘመኖች በስተቀር ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ጠንካራ መለያዎችን ተጋርተዋል፡፡ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ልዩነትም ቢሆን ቆለኛው ከደገኛው፣አርሶ-አደሩ ከአርብቶ-አደሩና ከነጋዴው ጋር በኢኮኖሚ ተደጋግፈው በባህል እየተወራረሱ ለዘመናት ኖረዋል፡፡ ገዳማት፣ አድባራትና መስጊዶች እንዲሁም የማህበረሰብ ተቋማትና የሰፈር ሽማግሌዎች ተቃራኒ ፍላጎቶችን በማስታረቅ ረገድ ለወደፊት የሚበጁ ሰላማዊ አደራዳሪ ተቋሞችን የምንገነባበት የባህል ቅርስ አጎናጽፈውናል፤
• ኢትዮጵያ በአፈ-ታሪክ ብቻ ሳይሆን የረጅም ስልጣኔዋ መለያ በሆነው የሥነ-ጽሁፍ ታሪኳን (ፊደሎቿን) በመጠቀም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሞራል፣ የፖለቲካ እና የቁሳቁስ ባህሎችዋን ስታስተላልፍ የኖረች አገር ናት፡፡ ከውጭ ስልጣኔዎች ጋር ባላት ግንኙነት ጭፍን ኩረጃ ሳይሆን የሚበጇትን ተቀብላ በረቀቀ ዘዴ ከባህሏ ጋር አጣጥማ የማስፋፋት ችሎታ የነበራትም አገር ናት፡፡ ለምሳሌ የሃይማኖት ገጽታን በሚመለከት፣ ከሌሎች አገሮች የሚለያት አርማዋ ከኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን ጋር የተጣመሩ የአይሁዳዊ፣ የክርስትናና የእስልምና እምነቶች አብረው ለብዙ ዘመናት በሰላም መኖራቸውን ነው፡፡ እንዲሁም
• የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦርነትና የፖለቲካ ሽብሮችና ውጥንቅጦች ጠባሳዎች ይታይባታል፡፡ ከነዚህም በኢጣሊያ ሁለት ጊዜ የተፈፀመባት ወረራዎችና ከዚያ ማግስት የተማከለ መንግስታዊ ቢሮክራሲ ለመፍጠር የተካሄዱ ሹኩቻዎች፣ በ1966 ዓ.ም በአብዮት ስም ሶሻሊዝም የተሞከረበት የመከራ ዘመን፣ በኤርትራ መዋሃድና እንደገና መገንጠል ወቅት የተካሄዱት የእርስ-በርስ ጦርነቶችን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡
የነዚህ አስከፊ ጥቃቶች ውጤቶችና ፍልሚያዎች ብዙ ናቸው፤የርስ-በርስ መተማመን መቦርቦር፤ በአንዳንድ ወጣት ዜጎቻችን አስተሳሰብ ላይ በሃገር ከመኩራት ይልቅ ወደ ማፈር ቀስ በቀስ መለወጥ፣ የድህነት መናርና የወጣቱ ተስፋ ማጣት፣ ቡድናዊነትና ወገናዊነት በግልጽ የሚታዩ ችግሮች ሲሆኑ እስካሁን ድረስ መፍትሄ አልተበጀላቸውም፡፡
በየወቅቱ የስርአቱ ካድሬዎች ጠብና ግጭት ማስወገጅያ ባህላዊ ልማዶችን በማጥፋትና ሽማግሌዎችን በመወንጀል ሕዝቡ በሃገር ሽማግሌዎች እና በመንግስት ሹማምንቶች ላይ ምንም አይነት እምነት እንዳያሳድር አድርገውታል፡፡
ይህ ስር እየሰደደ የመጣው የአስተሳሰብ እና የአመለካከት ቀውስ ጎላ ወዳሉ ሁለት ድምዳሜዎች ላይ ያደርሰናል፡፡

1ኛ) የምንገነባውን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በባለቤትነት እንድንቀበለውና እንድንኮራበት ከተፈለገ ጥራት ባላቸው የመንግስታዊ ስልጣን አያያዝ ባህሎቻችን ላይ የተመሰረተ መሆን እንደሚኖርበትና፤

2) ለዘላቂ ብልጽግና፣ የዜጎችንም ሆነ የመንግስትን ሉዓላዊነቶች ለማስከበርና ለአፍሪካ ቀንድ መሪነትን ለመጎናጸፍ ከውጭው ዓለም ጋር በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ ትስስር ሲዘረጋ መሆኑን ነው፡፡ የጋራ እድልን በጋራ ለመወሰን የሚያስችለንም ነው፡፡
በአይበገሬነት የቆየውና ቢወድቅ ነጥሮ የሚነሳው ኢትዮጵያዊ ክብር እና ጨዋነት ወደፊት ፍትሃዊነት የሰፈነበትን የመንግስት አወቃቀርና አሰራር ለመዘርጋትና “የነፃ-ዜጋ” ልደትን ለማብሰር እንደመሰረት ልንጠቀምበት ያስችለናል፡፡ ነፃ ዜግነት የጋራ ጥቅምን ከግል ጥቅም ጋር አጣጥሞ የሚያራምድ የልበ-ሙሉ እና የኩሩ ኢትዮጵያዊ መለያና አርማ ነው፡፡
የኢትዮጵያን ትንሳኤ በሚመለከት ይህ ሰነድ የሚያራምደውን ፅንሰ-ሃሳብ የሚያሳዩ ሦስት ዋና ዋና መሰረታዊ መርሆች ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህም፣
1) የሕዝብ ውክልና እና አለኝታ ያለበት አስተዳደር፣
2) ብዙሃኑ የአናሳዎችን መብት የሚያከብሩበት እና
3) የኢኮኖሚ ነፃነት ናቸው፡፡
እነዚህ መሠረታዊ መርሆዎች ተጨባጭ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተሀድሶ ዕቅዶችን ለመንደፍ የሚያገለግሉ ምስሶዎች ይሆናሉ፡፡ ሦስቱ የማይነጣጠሉ መሠረታዊ መርሆዎች ለዘላቂ ሰላም፣ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ማንነትንና በፍትሐዊ መንገድ የህዝብ ባለስልጣንነትን ያንፀባርቃሉ፡፡
ክፍል ፫
የኢትዩጵያ የሕዝብ አስተዳደር መለያ ምን ምን ናቸው?
ነፃነት መሰረታዊ ትርጉሙ ብዙ አማሪጮችን ማግኘት ሲሆን፤ ለፍትሐዊ የህዝብ አስተዳደር ቅድመ መሰረቱ ነው፡፡ ዲሞክራሲ ደግሞ መሰረታዊ ትርጉሙ ነፃ ሕዝብ የመምረጥ መብቱን በስራ ላይ የሚያውልበት የውሳኔ መስጫ መንገድ ነው፡፡ በህዝብ ሉዓላዊነት የተመሰረቱ ወኪላዊ የዲሞክራሲ ይዘቶች–ግለሰባዊ (ሊበራል) እንዲሁም ወልአዊ (ሶሻል)–የዜጎችን መብቶችን (ማለት ህይዎትን፣ ነጻነትን፣ ሃብትን) በውክልና በማስከበር ደረጃ አብነትን የያዙ ናቸው፡፡ የዚህም መሰረቱ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያገኙትን መብቶች ያካተተ ርዕስ-ሕግ በጽሁፍ ማጽደቅ ነው፡፡ ለዚህም ነው ይህ የቃል-ኪዳን ሰነድ መልካም የሆኑ ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና ልንዘነጋቸው የማይቻለን የዘመናችን እውነታዎችን ያካተተ ርዕስ-ሕግ እንዲዘጋጅ የሚጠይቀው፡፡
ስለ አገራችን ዲሞክራሲ ያለን አመለካከት በአገሪቷና በሌሎች ተመሳሳይ አገሮች የፖለቲካ ታሪክ ልምዶችና ተሞክሮዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተጫኑብን ሶስቱ ህገ-መንግስቶች ይህ ነው የሚባል ፍትህ፣ እኩልነትና ብልፅግና አለማስገኘታቸው ግልጽ ነው፡፡ በብልጣ-ብልጥ ገዢዎች እጅ የሕዝብ ማደናገሪዎች ከመሆን አላለፉም፡፡ ነገር ግን በወረቀት ላይ የተቀመጡ ተገቢ መብቶች ይዋል ይደር እንጅ ሕዝቡ ሲነቃ እንዲከበሩለት ስለሚታገል ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ቀስ በቀስ ሥር መስደድ ቋሚነታቸውን መርሳት ስህተት ነው፡፡
ከተሞክሮ እንደተማርነው እንከን-የለሽ የወረቀት ርዕሰ-ህግ በግብር ላይ መዋል የሚፋጠነው ትብብርንና የጋራ ኅላፊነትን ሳይታክቱ ለመብት ዘብ የመቆም ፈሊጥን ማዳበር ነው፡፡ በሰለጠኑት አገሮች ያንዱ መብት መገፈፍ የሁሉም መብት እንደመገፈፍ የሚቆጠረው አፍንጫ ሲመታ ዓይን ማልቀሱ አይቀርም እንደሚባለው ነው፡፡ ይኸ ባሕል በአገራችን ገና ጮርቃ ነው፡፡ ስለሆነም፣ ለጊዜው ምሽጋቸው በከተሞች የተወሰነው የፖለቲካ ድርጅቶች የገጠሩን መራጭ ማንቃትና መልሶም ከዚህ ሰፊ ሕዝብ ብልህ አስተሳሰብ መማር ግዴታቸው ነው፡፡
ማንኛውም የመንግስት አስተዳደር መብቶችን ሲጥስ እያንዳንዱ ዜጋ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲችል በዓለም-አቀፍ ደረጃ የሚሰራባቸው ስሌቶች በስነ-ስርዓት እንዲመዘገቡለት መጣር አለበት፡፡ ይህ ቃል-ኪዳን የሚደግፈው ርዕሰ-ሕግ በሰብዓዊነታቸውና በዜግነታቸው ብቻ የሚገቧቸውን መብቶች ለጊዜው ስልጣን የያዘ አስተዳደር ሊጥሳቸው እንደማይችል በማያሻማ መንገድ የሚያስቀምጥ መሆን አለበት፡፡ እነዚህ መብቶች ከበደልና ከፍርሃት ነጻ መሆንን፣ የሕግ የበላይነት መስፈንን፣ የማስብና ሃሳብን በነፃነት መግለጽን፣ በአብይ የአገሪቱ ጉዳዮች ውሳኔ ላይ ተሳታፊ መሆንን፣ ከችጋርና ድንቁርና ነጻ መሆንንና በሁሉም መስክ እኩል መብት ማግኘትን የሚያካትቱ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚገባትን ርዕሰ-ሕግ ሙሉ ይዘት በቅድሚያ ለመዘርዘር የዚህ የቃል-ኪዳን ሰነድ አላማም ሃላፊነትም አይደለም፡፡ ዳሩ ግን በውል ሊታሰብባቸው የሚገቡ አንዳንድ መሠረታዊ መመሪያዎችን ልንጠቅስ እንወዳለን፡፡ በዚህም መሠረት በዜጐችና በመንግሥት መካከል በግልጽ ውል ሆኖ የሚያገለግል ርዕስ-ሕግ፡-
• በከፍተኛ የሕዝብ ውክልናና ተሳትፎ የሚዘጋጅ፣
• ለሁሉም ዜጐች የፖለቲካ እኩልነትን የሚያረጋግጥና፣
• የሴቶችን ተሳትፎ የሚያበረታታና ሃላፊነትን የሚያጐናጽፍ፣
• መሰረታዊ የኑሮ ፍላጎቶች ካልተሟሉ ሌሎች መብቶች ሁሉ ምንም ፋይዳ ስለማይኖራቸው የነዚህን መብቶች አውራነት የሚያረጋግጥ፣
• ዜጐች በመንግሥት ላይ ያላቸውን የመምረጥ እና እያገለገለኝ አይደለም ብለው ባመኑበትም ወቅት በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን የማውድ ሥልጣን በግልጽ የሚያስቀምጥ፣
• የሕግ የበላይነትን የማክበር ባህል በሕዝብና በባለስልጣኖች ዘንድ ሙሉ በሙሉ እንዲሰርፅ የሚያመቻች፣
• የግለሰብ መብቶችን በማይጥስ መንገድ ሁሉንም ባህሎች ካለአድልዎ የሚያጠናክር፣
• ግልፅና አስተናጋጅ ማህበረሰብንና በውድድር ላይ የተመሠረተ የገበያ ኢኮኖሚ ስርዓትን የሚያጎለብትና እንዲሁም
• የመንግሥት ሥራ አገልግሎትን በተመለከተ ግልፅነት፣ ታዛዥነትና ታማኝነት እንዲሰፍኑ ሁኔታዎችን የሚያመቻች መሆን ይኖርበታል፡፡
የምናምንባቸውን መርሆዎች በተግባር ልንተረጉማቸው ይገባል፡፡ ለዚህም ሲባል ነው የፖለቲካ ሥርዓት በህግ የበላይነት ስር እንዲሰፍን የግለሰቦችንና የነፃ ድርጅቶች ንቁ ጥበቃ የማያስፈልገው፤ አምባ ገነኖችም እነዚህን የመብት ሐዋርያዎች ምርኮኛ አድርገው ስልጣናቸውን በሰላማዊ መንገድ ለሕዝብ ለማስረከብ ፈቃደኛ የማይሆኑት፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ርእሰ-መንግስትን በባለቤትነት የሚያቅፈው ዘላቂ ሰላምን፣ የህግ የበላይነትንና ፍትሕን አራማጅ ሆኖ ሲያገኘው ነው፡፡ ስለዚህ አዲሱ ርእሰ-ሕግ ሲረቅ ካለፉት ዘመናት ከተደረጉት ጥረቶችና ልምዶች የተገኙ ትምህርቶችን ያካተተና ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሠረታዊ መመሪያዎች ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት የቃል-ኪዳን ሰነዱ ያምንበታል፡፡ ስለዚህ ተረካቢውና ተከታዩ ትውልድ በባለቤትነት የሚጎናጸፈው መንግስታዊ ስርዓት የሚከተሉትን ይዘቶች ማንፀባረቅ ይገባዋል እንላለን፡-
(ሀ) የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ግዛት ማስከበር፡-
የኢትዮጵያ ሕዝብ በረዥም ታሪኩ ነፃነቱንና አንድነቱን ጠብቆ በማቆየት በዘር በቋንቋ በሃይማኖት ሳይከፋፈል በማህበራዊ አሩ በቀላሉ የማይበጠስ ዝምድናና ትስስር ፈጥሯል፡፡ በዚህ ሁሉ የታሪክ ሂደት ውስጥ ታዲያ ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ሃገራችንን ዳርድንበሯን እና ሉአላዊነቷን በማስጠበቅ ቀደምት አባቶቻችን ለሃገራቸው ክብር ሲሉ የከፈሉትን መስዋእትነት በማሰብ እና በመዘከር ለቀጣይ ትውልድ በማስተማር እና በማሳወቅ አዲሱ ትውልድ በሀገሩ እና በማንነቱ የሚኮራ እንዲሁም በሀገሩ ሉአላዊነት እና ዳር ድንበር ላይ ምንም አይነት ድርድርና ሰጥቶ መቀበል የሚል አስተሳሰብ እንዳይኖረው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሰውም አንፈልግ የኛንም አንሰጥ የሚለው የዘመናት እምነታችን እንደመለያ ለትውልድ ሊተላለፍ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያና ጐረቤቶቿም የቀጠና ውል በማጽደቅ ቋሚ ሰላምንና ለጋር ጥቅም መዛመድን ማጠናከር ይበጃቸዋል፡፡
(ለ) የግለሰብ መብቶች ቀደምትነት፡-
የዲሞክራሲ ስርዓት ይዘት የሚመነጨው ከግለሰብ መብት ስለሆነ ነፃ ግለሰቦች የሚኖሩበት አገር ደግሞ በምንም መልኩ የቡድንን መብት ሊያፍን የሚችልበት አካሄድ ስለማይፈጥር የብዙሀኑን ጥቅምና የጥቂቶችን መብት ማስከበር በሚችል መልኩ የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይህም ሲሆን ግን ማህበረሰቡ የሚጸየፋቸውን ነውሮችን እና ጎጂ ልማዶችን እውቅና አይሰጣቸውም፡፡ “አንድ ዜጋ አንድ ድምፅ” ባለበት የአስተዳደር ሥርዓት፣ ግለሰቦች የፈለጉትን ድርጅት መደገፍ ከመቻላቸውም ሌላ ባህላዊም ሆነ ሃይማኖታዊ እሴቶቻቸውን ማክበርና ማጎልበት በሚያስችል መልኩ መብትን ያጎናጽፋቸዋል፡፡ ይህም ሲባል ዴሞክራሲ የብዙሃንን ፍላጎትን ብቻ የሚያስተናግድ ሳይሆን የአናሳ ቡድኖችንም መብት የሚያስከብር ስርዓት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
(ሐ) ለሕልውና መሰረታዊ ፍላጎቶችን የማግኘት ዋስትና፡-
በቂ ምግብ መጠለያና ልብስ ማግኘት የህልውና መስረት ስለሆነ እንደ መሰረታዊ መብት ተቆጥሮ መንግስታት ለዜጎቻቸው የማሟላት ሃላፊነታቸው ብቻ ሳይሆን ግዴታቸውም መሆኑን አምነው ሲተገብሩት ይታያል፡፡ ስለዚህ በሃላፊነት እና በተጠያቂነት ሕዝብን የሚያገለግል መንግስት (ምንም ደሃ ቢሆን) በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቹ በረሀብ እያለቁ፤ ህፃናት በምግብ እጥረት በረሃብ ህይወታቸው ሲቀጠፍ እና በቀላሉ ሊወገዱ በሚችሉ በሽታዎች ሲጠቁ እያየ እንዳላየ የሚያልፍ ህሊና ሊኖረው ስለማይችል ማንኛውም በህዝብ ይሁንታ የተሰየመ መንግስት እነዚህን መሰረታዊ መብቶች የማሟላት ግዴታ ይኖርበታል፡፡
(መ) የሃገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ(ዎች) እንዲኖር ማድረግ
ሐገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ዜጎች ያሉባት ሃገር እንደመሆ መጠን ህዝቧ ተከባብሮና ተፋቅሮ የመኖሩ ባህላችን እንደተጠበቀ ሆኖ ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት ይኖርብናል፡፡ ይህ በመሆኑ ምክንያት ሁሉም የሃገሪቷ ዜጎች በየአካባቢያቸው የሚጠቀሙበትን ቋንቋቸውን የመጠቀም እና የማዳበር መብታቸው እንደተከበረ ሆኖ የሀገሪቷ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማቀላጠፍ የብሔራዊ ቋንቋ(ዎች) መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
(ሠ) የመሬት ባለቤትነት መብትና ዋሰትና
የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ከዜግነት ጥያቄ እኩል ሆኖ መወሰድ አለበት፡፡ ስለሆነም መሬት የግለሰብ መሆን ይኖርበታል፡፡ በግለሰብ ይዞታ ስር ያልሆነ እና በወል ያልተያዘን መሬት መንግስት በአደራ የማስተዳደር ኃላፊነት ሊኖረው ይገባል፡፡
(ረ) ያልተማከለ መንግስታዊ ስርዓት፡-
ያልተማከለ መንግስታዊ ስርዓት ሲባል በሀገሪቱ የሚዋቀሩ የራስ ገዝ ክፍላተ ሀገራት የሚኖሩትና አሃዳዊ ያልሆነ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ክፍላተ ሀገራት ታሪካዊ ትስስርን እና መልካዓ-ምድራዊ አቀማመጥን ከግምት የሚያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡ መንግስታዊ አውታሮች የእርስ በእርስ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ሆነው መዋቀር ይገባቸዋል፡፡
(ሰ) ሁሉን-ወካይ የፍትህ፡ የወታደርና የሲቪል አገልግሎቶች፡-
መሠረታዊ መብቶች ሊጠበቁ የሚችሉት የሀገሪቱን ማኅበረሰብ ጥቅምና ፍላጎት የሚወክሉ በችሎታቸው የሚመረጡ የወታደር፣ የሲቪልና የደህንነት አገልግሎቶች ሲቋቋሙ ነው፡፡ እነሱም ሁለት መመሪያዎችን ማክበር አለባቸው፡-
1ኛ) የሲቪል አስተዳደሩ፤ የወታደራዊው ተቋም እና የደህንነትና የጸጥታ ተቋማት የስራ ድርሻቸው በግልጽ በህግ የተደነገገ መሆን ይኖርበታል፡፡
2ኛ) ሁሉም መንግስታዊ ተቋማት በመካከላቸውም ሆነ ከዜጎች ጋር ቅራኔዎች በሚፈጠርበት ወቅት በህግ ፊት እኩል እና ያለምንም ጣልቃገብነትና አድሎ የፍትህን የበላይነት የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
(ሸ) ነፃና ፍትሃዊ የገበያ ስርዓት፡-
ማንኛውም ዜጋ የግል ንብረቱ ሕጋዊ ዋስትና አግኝቶ በፈለገበት የአገሪቱ ክፍል የመኖር፣ የመስራት፣ በነፃ ገበያ ተወዳድሮ የማምረትና የማትረፍ መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል፡፡ ውድድር ያለበት የገበያ ስርዓትን ለመገንባት መንግስት ከሚፈጽማቸው ሃላፊነቶች መካከል ዋነኞቹ አድልዎ የሌለበት የውድድር ሥርዓት መፍጠር እና ዋጋን ማረጋጋት ናቸው፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች በየትኛውም መልኩ የንግድ ስራ ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ አይችሉም፡፡ በፓርቲ የተያዙ የንግድ ኩባንያዎች ካሉ ወደፊት በሃገሪቱ የፍትህ ስርአት አማካኝነት አግባብ ያለው ውሳኔ ይሰጥባቸዋል፡፡ መንግስት በየትኛውም መልኩ ከፍርድ ቤቱ የፍትሕ አካካት ውሳኔ ውጪ ተsማቱን ወይም ኩባንያዎቹን የማገድ፤ የመዝጋት፤ የመውረስ ወይም የማዋሃድ ስልጣን አይኖራቸውም፡፡
(ቀ) ነፃና ተጠያቂ የሲቪክ ማህበራት እና የፖለቲካ ፓርቲ ተቋማት፡-
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ውስጥ በተለይም የዝቅተኛውን የማህበረሰብ ክፍል በአጋርነት የሚያገለግሉ በርካታ የሙያ፣ የርዳታ፣ የምሁራን፤ የጋዜጠኞችና የሲቪክ ድርጅቶች አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ በተለይም ስርዓት አልበኝነት ለመግታት ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፡፡ ይህም በመሆኑ ምክንያት ማህበራት ከማንኛውም አይነት ተፅዕኖዎችና አፋኝ ሕጎች ነጻ በሆነ መልኩ የመንቀሳቀስ እና የመስራት መብታቸው በህግ ሊጠበቅላቸው ይገባል፡፡
የፖለቲካ ድርጅቶች መሠረታዊ አላማቸው መንግስታዊ ስልጣንን ለመጎናፀፍና በሃገሪቱ ሃብት አያያዝ ላይ ያላቸውን ፖሊሲ ለማስፈጸም ነው፡፡ ይኸ ሁኔታ ሁለት ጉዳዮችን ያስነሳል፡፡
አንደኛው– ለህዝብ የቆሙትን ወይም በዲሞክራሲያዊ መንገድ በህዝብ የተመረጡትን ለመለየት የጠራ የፖለቲካ የውድድር ስርዓትን መዘርጋት ሲሆን
ሁለተኛው፡- የተመረጠ ፓርቲ ወደ ሙስናና አምባገነንነት እንዳያዘቀዝቅ ማነቆዎች ሆነው የሚያገለግሉ አድልዎ አልባ ተቋሞችን ማጠንከር ነው፡፡
ስለሆነም የሲቪክ ማህበራትን መንከባከብና ንቅናቄዎቻቸው የአገርን እና የህዝብን ጥቅም እስክልተጋፋ ድረስ ማበረታታት አስፈላጊ ነው፡፡
ክፍል ፬
የዲሞክራሲ እድገትና የሲቪክ እንቅስቃሴ መንታነት
የዚህ ቃል ኪዳን ይዘት ለሕዝብ ከሚቀርቡ የተለያዩ የፖለቲካ ስርዓቶች ጋር አይጋጭም፡፡ ዋነኛው ጥሪ ኢትዮጵያዊያን ካለምንም ተጽዕኖ ከዘመኑ ምኞታቸውና ከክብር ባህላቸው ጋር የሚጣጣመውን የአስተዳደር ስርዓት የመምረጥ መብታቸው ይጠበቅ የሚል ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈጥሮ ባህሪያቸው ስልጣን ለመጎናፀፍ በመሆኑ እድልዎ-አልባና የተደላደለ የውድድር መስክን ለማመቻቸት ነው፡፡ የፖለቲካና የህግ ተቋሞች ግንባታ ትክክለኛ ፈር እስከያዘ ድረስ የሕዝብ አለኝታ በእነዚህ ተቋዋማት ላይ በአንድ ጊዜ የሚፈጠር ሳይሆን በሂደት መዳበር እንደሚኖርበት ማስታወስ ለትግስት ይረዳል፡፡
የአሁኑ ትውልድ በዓለም ነፃ ሕዝቦች ማህበረሰብ ውስጥ የሚገባውን ቦታ እንዲያገኝ ለማድረግና የእጣውን ባለቤትነት ለማሳወቅ ቋሚ የነፍስ-ወከፍ እንቅስቃሴ ማድረግ ዋና ቁልፍ ነው፡፡ ምንግዜም የማይታክቱት የኢትዮጵያ ልጆች መብታቸውን ለማስከበር “አገርህን አድን” ርብርብ ላይ ቸል እንደማይሉ እምነታችን ነው፡፡

ኢትዮጵያ በልፅጋና በልጆችዋ ተከብራ በነፃነት ለዘለዓለም ትኑር!

Posted in politics | Leave a comment

ያገሬ ሰውና ያገሬ መንግስት ይመሳሰላሉ፤ ራሳቸውን ጠልፈው መጣል ይቀናቸዋል

◾ተመራቂ ወጣቶችን ወደ ቢዝነስና ወደ ሥራ ፈጠራ ለማነሳሳት የሚጣጣር መንግስት፤ የቢዝነስ ሰዎች “አጭበርባሪ፣ ስግብግብና ኪራይ ሰብሳቢ ናቸው” እያለ ያንቋሽሻቸዋል። እዚያው በዚያው የራሱን ጥረት ራሱ ያመክነዋል።
◾. አገሪቱ ከድህነት ተላቃ ማደግ የምትችለው በትርፋማ የቢዝነስ ሰዎች ጥረት ነው የሚል መንግስት፤ የራሱን ንግግር ራሱ ያፈርሰዋል። ትርፍ ለማግኘት መስራትን ያብጠለጥላል – “የማስቲካና የከረሜላ አስመጪ” እያለ።
◾. ሕይወቱ እንዲሻሻልና ኑሮው እንዲበለፅግ የሚመኝ ብዙ ሰው፤ ራስ ወዳድነትን ሳይሆን መስዋእትነትን፣ ከትርፋማነት ይልቅ ምፅዋትን ያወድሳል። ራሱን ያልወደደና ትርፋማነትን ያላከበረ ሰው እንዴት ሕይወቱን ያሻሽላል?
◾. መንግስትን የማያምን የአገሬ ሰው፤ “ነጋዴዎች፣ የሸቀጥ እጥረትንና የዋጋ ንረትን ይፈጥራሉ” በሚለው ውንጀላ መንግስትን ሙሉ ለሙሉ ያምናል – እጥረት የተባባሰው በመንግስት የተያዙት ስኳር፣ ዘይትና ስንዴ ላይ ቢሆንም።

በአንድ በኩል፤ ስለ ብቃትና ስኬት ማውራት
እየተለመደ መጥቷል – ቢዝነስና ትርፋማነት፣ ሥራ ፈጠራና ኢንዱስትሪ፣ ሃብት ፈጠራና ብልፅግና… ዘወትር ስማቸው እየተደጋገመ ይነሳል።
በሌላ በኩል ደግሞ፤ ስኬት፣ ትርፋማነትና ሃብት ፈጠራ እየተንቋሸሹ፣ ምስኪንነት፣ ምፅዋትና አገልጋይነት ሲሞገሱና ሲወደሱ እንሰማለን። አዲስ ነገር አይደለም። “የዚህ አለም ደስታና ብልፅግና ረብ የለሽ አላፊና ረጋፊ ነው” ከሚለው ጥንታዊ የውድቀት ባሕልና አስተሳሰብ አልተላቀቅንም። ይህም ብቻ አይደለም። በዚሁ ኋላቀርነት ላይ፤ ባለፉት አርባ ዓመታት ሌላ መርዝ ተጨምሮበታል። “ከራሴ በፊት ለሰፊውና ለድሃው ሕዝብ መስዋእት ልሁን” የሚል የሶሻሊስቶች መፈክር፤ “ከራሴ በፊት ለእናት አገሬ፣ ለብሔር ብሔረሰቤ” የሚል የፋሺስቶች መዝሙር፣ ይሄውና አሁንም ድረስ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ስሜት ይኮረኩራል።
ምናለፋችሁ! ሁሉም ነገር የተቀየጠ ሆኗል፡፡ ስለ ብቃትና ስለ ስኬት የሚያወራ ሰው፤ ዞር ብሎ ምስኪንነትንና መስዋዕትነትን ያዳንቃል። ሃብት ፈጠራንና ቢዝነስን አበረታታለሁ የሚል መንግስት፤ ዞር ሳይል ባለሃብቶችን በሰበብ አስባቡ እየወነጀለ ቁምስቅላቸውን ያሳያቸዋል፤ “የሃብት ክፍፍል” እያለ በፖለቲካ ቋንቋ ጥንታዊውን የምፅዋት አምልኮ ይሰብካል። ሁለት ሱሪ ያለው አንዱን ያካፍል እንዲሉ፡፡
እናላችሁ፣ ራስን ጠልፎ የመጣል አባዜ የበረከተበት ግራ የተጋባ ዘመን ላይ ነው ያለነው። እየገነቡ የማፍረስ በሽታ! ብልፅግናን እየፈለጉ ራስ ወዳድነትን የማብጠልጠል ልክፍት! ይህንን በግልፅ የሚመሰክሩ አራት የሰሞኑ ዜናዎችን እጠቅስላችኋለሁ።

1. ተመራቂዎች ቢዝነስን ወይም አገልጋይነት?
ዘንድሮ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚመረቁ ከ50ሺ በላይ ወጣቶች፣ ከመንግስት ሳይጠብቁ፤ በራሳቸው መንገድ ሕይወታቸውን የሚያሻሽል ሥራ (ቢዝነስ) እንዲፈጥሩ ምክርና ማሳሰቢያ ከመንግስት ባለስልጣናት ሲጎርፍላቸው ሰንብቷል። ቀላል ምክር አይደለም። ጉዳዩ፤ የድህነትና የብልፅግና፤ የሞትና የሕይወት ጉዳይ ነው – ለእያንዳንዱ ወጣት። ስንቱ የጨነቀው ወጣት፣ ድንበርና እየዘለለ፣ ኬላ እየሰበረ፣ የበረሃውን ንዳድ የባህሩን ውርጭ እያቆራረጠ የሚሰደደው ለምን ሆነና! ጉዳዩ፤ የኢኮኖሚ እድገትና የኢኮኖሚ ቀውስ ጉዳይ ነው – ለመንግስት። በየአቅጣጫው በርካታ አገራት ሲተራመሱ የምናየው፣ በርካታ መንግስታት ሲቃወሱና ሲፈናቀሉ የምንመለከተው ለምን ሆነና! የጎሰኝነት ጡዘትና የሃይማኖት አክራሪነትን ጨምሮ፤ ከዘመናችን ሶስት ዋና ዋና ቀውሶች መካከል አንዱ፤ ወጣቶችን ተስፋ የሚያስቆርጥ የኢኮኖሚ ቀውስ ነው – በገናና የሚፈጠር የቅይጥ ኢኮኖሚ ቀውስ፡፡ እናም፤ ተመራቂ ወጣቶች ለስራ ፈጠራና ለቢዝነስ እንዲነሳሱ፣ ከመንግስት በኩል ምክርና ማሳሰቢያ እየተደጋገመ ቢሰነዘር አይገርምም። ብልህነት ነው፤ የህልውና ጉዳይ ስለሆነ።
ታዲያ፤ ተመራቂዎቹ ወጣቶች ይህንን እጅግ ትልቅ ምክር ሰምተው፤ የራሳቸውን ቢዝነስና ንግድ ቢፈጥሩ፣ አድናቆትና ክብር ያገኛሉ ማለት አይደለም። ጉዳዩ የሕይወትና የሞት፣ የብልፅግናና የቀውስ ጉዳይ ቢሆንም ያን ያህል ክብደት አይሰጠውም።
እንደ ትልቅ ነገር ተቆጥሮ ክብር የተለገሰውና በስፋት የተለፈፈው ጉዳይ ምን እንደሆነ ልንገራችሁ። በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፤ በክረምት ወራት ጊዜያቸውን ለህዝቡና ለአገር መስዋእት በማድረግ፣ ለበጎ አድራጎት ስራ ይሰማራሉ የሚል ዜና አልሰማችሁም?
በእርግጥም፤ የከፍተኛ ትምህርት አላማ፤ የራሳቸውን ቢዝነስ እየከፈቱ ራሳቸውን የሚጠቅሙ ተመራቂዎችን ማፍራት ሳይሆን፤ አገሪቱን በተለያዩ ሙያዎች የሚያገለግል የሰው ሃይል ማፍራት ነው – የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ። ያ ሁሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪ፤ በክረምት ወራት መስዋእትነት፣ አንዳች ጠብ የሚል ቁም ነገር አይሰራ ይሆናል። ዋናው ነገር፤ ለየራሳቸው በሚጠቅም ስራ ላይ ሳይሰማሩ የክረምቱን ጊዜ (መስዋእት ማድረጋቸው) ማቃጠላቸው ነው። ቢረባም ባይረባም፤ ለቢዝነስ ሳይሆን ለአገልጋይነት መሰማራታቸው ነው – አድናቆትን የሚያተርፍላቸው።
በአጭሩ፤ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ የመንግስት ጥገኛ ከመሆን ይልቅ በስራ ፈጣሪነት ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ መንግስት ማሳሰቢያ ሲሰጥ መሰንበቱ ብልህነት ነው። ተመራቂዎች ሥራ መፍጠር ካልቻሉ፤ ሥራ አጥነትና ተስፋቢስነት እየተስፋፋ አገሪቱ ልትቃወስ ትችላለቻ። ይህን አደጋ በመገንዘብ፤ ተመራቂዎች የየራሳቸውን ሕይወት ለማሻሻል ከሁሉም በላይ ለሥራ ፈጠራ ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው ሲመክር የሰነበተ መንግስት፤ ያንን ምክር ለማምከን ሲጥር መሰንበቱ ነው ችግሩ። የአገርና የህዝብ አገልጋይ መሆን ከሁሉም የላቀ ክብር እንደሚገባው በመግለፅ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የክረምት ጊዜያቸውን “ለበጎ አድራጎት ሥራ” መስዋእት እንዲያደርጉ መንግስት አሰማርቷቸዋል። ራስን ጠልፎ የሚጥል ቅይጥ አስተሳሰብ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡

2. የመንግስት የጅምላ ንግድ – ነጋዴዎችን ለማበረታታት ወይስ ለመጣል?
መንግስት፣ ሶስተኛውን የጅምላ ንግድ ማዕከል በመርካቶ ሲከፍት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ዋና አማካሪ አቶ ነዋይ ገብረአብ፤ የግል ባለሃብቶች ወደ ዘመናዊ የጅምላ ንግድ እንዲሸጋገሩ ለማሳየትና ለማነሳሳት ይጠቅማል ብለዋል። የጅምላ ንግድ በመንግስት ሳይሆን በባለሃብቶች እንዲካሄድ እንፈልጋለን ሲሉም ተናግረዋል። (አማካሪው ለምን እንዲህ አሉ? የባለሃብቶች የግል ኢንቨስትመንት፣ ኢኮኖሚውን የሚያንቀሳቅስ ዋነኛ ሞተር ነው። የቢዝነስ ሰዎች ሃብትን ይፈጥራሉ፤ ራሳቸውን ለመጥቀምና ትርፍ ለማግኘት ሲጣጣሩ፤ ሌላውም ሰው ይጠቀማል በሚል እምነት ነው)።
በሌላ በኩል እስከአሁን ሶስት የመንግስት የጅምላ ንግድ ማዕከላት እንደተከፈቱና ተጨማሪ ማዕከላትን በመክፈት አገልግሎቱ እንደሚስፋፋ የገለፁት የንግድ ሚኒስትር፤ ዋነኛ አላማው በነጋዴዎች አማካኝነት የሚፈጠረውን የሸቀጥ እጥረትና የዋጋ ንረት መከላከል እንደሆነ አስታውቀዋል። (ለምን የቢዝነስ ሰዎችን መወንጀል አስፈለገ? መንግስት በገፍ የብር ኖት ከማሳተም ከተቆጠበ ወዲህ የዋጋ ንረት ረግቧል – ከ2003 ወዲህ ። መቼም ቢሆን፣ የዋጋ ንረት የሚፈጠረው በመንግስት እንጂ በነጋዴዎች ወይም በቢዝነስ ሰዎች አማካኝነት አይደለም። እንዲያም ሆኖ፤ በተገኘው ሰበብ የግል ቢዝነስንና ንግድን መኮነን የአገራችን ነባር ባህል ነው። እናም መንግስት፣ “የግል ቢዝነስ፣ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዋነኛ የቀውስ አደጋ ነው። የቢዝነስ ሰዎች፤ ለአገር ልማት ሳይሆን ትርፍ ለማግኘት ይሰራሉ” በሚል እምነት ዘወትር ተመሳሳይ ውንጀላ ያዘንብባቸዋል)

3. ፎቀቅ ያላለውን ኢንዱስትሪ ለማነቃቃት – ባለሃብቶችን ማነሳሳት ወይስ ማብጠልጠል?
ባለሃብቶች ከንግድ ቢዝነስ ባሻገር፣ ወደ ማምረቻ (ወደ ማኑፋክቸሪንግ) የኢንዱስትሪ ቢዝነስ እንዲገቡ ለማነሳሳት፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በወዲያኛው ሳምንት ለሁለት ቀናት ገለፃ ሲሰጡ ውለዋል። ለምን? የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ በሚል ያዘጋጁት ሰነድ እንደሚለው፤ በግል ኢንቨስትመንት እንጂ በሌላ መንገድ ስኬታማና ትርፋማ ፋብሪካዎችን ማስፋፋት አይቻልም። እናም ፋብሪካዎች በትርፋማነት እንዲስፋፉና እንዲያድጉ፤ የስራ እድሎች በብዛት እንዲከፈቱ ከተፈለገ፤ የቢዝነስ ሰዎች በዚሁ መስክ እንዲሰማሩ ማግባባት ያስፈልጋል – የተለያዩ እንቅፋቶችንና መሰናክሎችን በማስወገድ።
የማኑፋክቸሪንግ ቢዝነስ፤ አርቆ አሳቢነትንና ፅናትን፣ ለአመታት የሚዘልቅ ጥረትንና የፈጠራ ትጋትን ይጠይቃል። ይህንን የማሟላት ችሎታ ያላቸው ደግሞ የመንግስት ቢሮክራቶች ሳይሆኑ የቢዝነስ ሰዎች ናቸው። በወዲያኛው ሳምንት የተዘጋጀው ገለፃም ከዚሁ እምነት ጋር ይያያዛል። የመንግስት ባለስልጣናት እንዲህ አይነት እምነት ከያዙ፤ “እውነትም ለቢዝነስ ስራና ለቢዝነስ ሰዎች ትልቅ ክብር አላቸው” ያስብላል። ግን፤ ወዲያውኑ አፍርሰውታል።
አክብሮትን ሳይሆን ተቃራኒውን ስሜት ለማሳየት ጊዜ ያልፈጀባቸው የመንግስት ባለስልጣናት፤ “የአገራችን ባለሃብቶች፣ በአጭር ጊዜ እና በቀላሉ ከፍተኛ ትርፍ ማግኘት ይፈልጋሉ” ሲሉ ከዘለፋ ወዳልተናነሰ ቅኝት የተሸጋገሩት በዚያው ገለፃ ላይ ነው። የንግድ ስራ ቀላል ነው? ቀላል ቢሆን፣ ለምን የመንግስት ባለስልጣናትና ቢሮክራቶች በንግድ ስራ አይሳካላቸውም? ለምን ደርግ አልተሳካለትም፣ ዛሬም መንግስት የገባበት የንግድ ስራ በሙሉ፤ በሙስናና በሸቀጥ እጥረት ሲበላሽ የምናየውኮ አለምክንያት አይደለም። የስንዴ እጥረት፣ የዘይት እጥረት፣ የስኳር እጥረት… እነዚህ በመንግስት የተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ፤ የንግድ ቢዝነስ ቀላል እንዳልሆነ የሚመሰክሩ ናቸው። የመንግስት ባለስልጣናት ይህንን የአደባባይ እውነት ለማገናዘብ ፍቃደኛ አይመስሉም።
ይልቁንስ ትርፋማነትንና ቢዝነስን የሚያንቋሽሽ ነባር የአገራችንን ባህል ይዘው ማራገብንና መዛትን መርጠዋል። የቢዝነስ ሰዎች በተለመደው የንግድ ሥራ “ኪራይ ሰብሳቢ” ሆነው ለመቀጠል እንጂ ወደ አምራች የኢንዱስትሪ ቢዝነስ ገብተው “ልማታዊ ባለሃብት” ለመሆን የማይፈልጉ ከሆነ፤ ብድር አያገኙም ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። “የቢዝነስ ሰዎች፣ በጥረት ሃብት መፍጠር አይፈልጉም። በቀላሉ ትርፍ ለማጋበስ እንጂ ለአገር ልማት አስተዋፅኦ የማድረግ ሃሳብ የላቸውም – ከረሜላና ማስቲካ አስመጪ ሁላ!” …
ራስን ጠልፎ መጣል፣ እየገነቡ ማፍረስ ይሏል ይሄው ነው ብሎ ማንኮታኮት ነው፤ የቅይጥ ኢኮኖሚ ባህርይ፡፡

4. የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ – የዋጋ ንረትን ይፈጥራል ወይስ አይፈጥርም?
ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ስለተጨመረ፣ የዋጋ ንረት እንደማይከሰት የገለፁት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር፤ የደሞዝ ጭማሪው በጥናት ላይ የተመሰረተና በበጀት የተያዘ ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል – ለደሞዝ ጭማሪ ተብሎ የብር ኖት ህትመት በገፍ እንደማይካሄድም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝም እንዲሁ፣ ተመሳሳይ መከራከሪያ በማቅረብ፣ የዋጋ ንረት የሚፈጠርበት አንዳችም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለም ብለዋል። በእርግጥም፤ መንግስት የብር ኖቶችን በገፍ ከማሳተም እስከተቆጠበ ድረስ፤ የዋጋ ንረት አይፈጠርም። ትክክል ነው። እንዲያም ሆኖ፣ በዚህችው አጋጣሚ፣ የቢዝነስ ስራንና የቢዝነስ ሰዎችን ሳይወነጅሉ ለማለፍ አልቻሉም። “ስግብግብ ነጋዴዎች የዋጋ ንረት እንዳይፈጥሩ ክትትልና ቁጥጥር ይካሄዳል፤ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል” በማለት ደጋግመው ተናግረዋል።
ዜጎች በሥራ ፈጠራና በምርታማነት ኑሯቸው እንዲሳካ፣ የቢዝነስ ሰዎች በትርፋማነት ኢንዱስትሪ እያስፋፉ እንዲከብሩ፤ በአጠቃላይ ለሃብት ፈጠራና ለብልፅግና ከፍተኛ ዋጋ እንደሚሰጥ የሚገልፅ መንግስት፤ የቢዝነስ ስራንና የቢዝነስ ሰዎችን ማጣጣል መደበኛ ስራው ሲሆን ምን ይባላል? “ራስን ጠልፎ የመጣል አባዜ” አይደለምን?
“ጥቃቅንና አነስተኛ” በሚል የተለያዩ የቢዝነስ ሥራዎችን የጀመሩ በርካታ ወጣቶች፣ “ገበያ አጣን” በማለት በተደጋጋሚ ለመንግስት አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ሳታውቁ አትቀሩም፡፡ መንግስትም፤ “የገበያ ትስስር እፈጥርላችኋለሁ” እያለ በርካታ ፕሮጀክቶችን ያለጨረታ ለዚህኛውና ለዚያኛው ሲቸር ቆይቷል፡፡ ግን ለሁሉም ጥቃቅን ተቋማት ከዓመት ዓመት ችሮታ ማዳረስ አይቻልም፡፡ “የገበያ ትስስር እፈጥርላችኋለሁ” የሚለው ፈሊጥ እንደማያዋጣ ቀስ በቀስ የተገነዘቡ ባለስልጣናት አሁን አሁን የሚሰጡት ምላሽ፤ “ከመንግስት ችሮታ የምትጠብቁ ጥገኞች መሆን የለባችሁም” የሚል ሆኗል።
እውነትም፣ የቢዝነስ ሰዎች እንጂ ቢሮክራቶች ለዘለቄታው የሚያዋጣ የገበያ ትስስር የመፍጠር አቅም የላቸውም። የቢዝነስ ሰዎች ገበያ የሚያገኙትና ትርፋማ የሚሆኑት ለምንድነው? አንዴ ሁለቴ፣ ይሄንን ወይም ያንን በማጭበርበር ለማምለጥ የሚሞክሩ የቢዝነስ ሰዎች መኖራቸው አያጠራጥርም። ነገር ግን፣ ብዙም አይራመዱም። ስኬታማ መሆን የሚችሉት፣ በተወዳዳሪነት ብቃት ነው። የመንግስት ባለስልጣናት ይሄንን አያጡትም። “ጥቃቅንና አነስተኛ” የቢዝነስ ተቋማትን ለሚመሰርቱ ወጣቶችም ይህንኑን ሲነግሯቸው ሰምተናል – “በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆነ ምርት ስታቀርቡ ነው ገበያ በማግኘት ትርፋማና ስኬታማ መሆን የምትችሉት” በማለት።
ይሄ ምክር፣ አማራጭ የሌለው ትክክለኛና የሚያዋጣ ምክር ነው። በሌላ አነጋገር፤ ዋጋ በማናር ለማትረፍ የሚሞክር ነጋዴ፤ ገበያተኛ እየሸሸው ይከስራል እንጂ አይሳካለትም። በሌላ አነጋገር፣ ነጋዴዎች የዋጋ ንረትን መፍጠር አይችሉም። ይህንን የሚያውቁና የሚናገሩ ባለስልጣናት፤ ዞር ብለው “ነጋዴዎች የዋጋ ንረትን ይፈጥራሉ” የሚል ውንጀላ ሲሰነዝሩ ምን ይባላል? በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ለተሰማሩ ወጣቶች የሰጡትን ምክር፣ መልሰው ይንዱታል። “እንዳሻችሁ ዋጋ በማናር ገበያ ማግኘትና ትርፋማ መሆን ትችላላችሁ” የሚል የውሸት ምክር እንደመስጠት ቁጠሩት – እውነተኛውን ምክር የሚያፈርስ።
በአጠቃላይ፤ ዛሬ ዛሬ ለወሬ ያህል ደግ ደጉን ማውራት ተጀምሯል። ብቃትና ስኬት፣ ትርፋማነትና ብልፅግና፣ ምርታማነትና ስራ ፈጠራ፣ መጣጣርና የራስን ሕይወት ማሻሻል የሚሉ ቃላት ባገሬ ሰዎች አንደበት ዘንድ እየተዘወተሩ ነው። የመንግስት ባለስልጣናትም እንዲሁ፣ ኢንቨስትመንትን መሳብ፣ ኢንዱስትሪን ማበረታታት፣ የገበያ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ እያሉ ሲናገሩ እንሰማለን። ጥሩ ነው። ግን “ወሬ ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡ የስኬት ወሬ፣ በተግባር የማይሳካው፤ አብዛኛው የአገሬ ሰውም ሆነ የመንግስት ባለስልጣናት፤ በገዛ አንደበታቸው ለሚናገሩት “የስኬት ሃሳብ”፤ እምብዛም ክብር ስለሌላቸው ነው። ከብቃትና ከስኬት ይልቅ፤ አቅመ ቢስነትንና ምስኪንነትን፤ ከትርፋማነትና ከብልፅግና ይልቅ ምፅዋትንና ችግር መጋራትን፤ ከስራ ፈጠራና ሕይወትን ከማሻሻል ይልቅ መስዋእት መሆንና አገልጋይነትን ያደንቃሉ – ያገሬ ሰውና ያገሬ መንግስት።
ከ“ትርፋማነት” እና ከ“ምፅዋት” መካከል የትኛውን ነው “በጎ አድራጎት” በማለት የምናሞግሰው? ያገሬ ሰው በአብዛኛው፤ የ“ምፅዋት” አወዳሽ ነው – “ሁለት ጫማ ያለው አንዱን ይመፅውት” ይባል የለ! መንግስትንም ብታዩት፣ ከዚህ የተለየ አይደለም።
መንግስት አገሬውን ይመስላል። መቼም፤ ለኢትዮጵያ ተብሎ፣ ከሌላ ፕላኔት ልዩ መንግስት አይመጣም። ያገራችንን መንግስትና ገዢ ፓርቲ ተመልከቱ። የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚፈልጉ ሌሎች ፓርቲዎችንና ፖለቲከኞችንም ጠይቋቸው። ባትጠይቋቸውም ይነግሯችኋል። ለድሆች የቆሙና “ለዝቅተኛው ሕብረተሰብ” የወገኑ መሆናቸውን በኩራት የሚናገሩት የአገራችን ፓርቲዎች፣ የምፅዋት አድናቂዎች ናቸው – ከራሳቸው ኪስ በማይወጣ ገንዘብ ድሆችን በመደጎም ተአምረኛ ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያልሙ።
ከሁሉም ፓርቲዎች አፍ የማይጠፋ፣ እንደ ፀሎት ቀን ከሌት የሚደጋግሙት “እጅግ የተከበረ ቅዱስ መፈክር” ቢኖር፤ “የሃብት ክፍፍል” የሚለው ፈሊጥ ነው። ያው “ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ይመፅውት” ከሚለው ስብከት ጋር ይመሳሰላል። ግን ይብሳል። “ምፅዋቱ” በፈቃደኝነት የሚፈፀም ሳይሆን በሕግ የታወጀ ግዴታ እንዲሆን ያደርጉታል። ለነገሩ፤ አቅመቢስነትንና ምስኪንነትን፤ ምፅዋትንና ጥገኝነትን አስበልጦ የመውደድና የማምለክ ጉዳይ ብቻ አይደለም። በተቃራኒው፤ ብቃትንና ስኬትን፣ ትርፋማነትንና ብልፅግናን የማጣጣል፤ ከዚያም አልፎ የማንቋሸሽና የማውገዝ ዝንባሌ ይታከልበታል። “ራስ ወዳድነት”ን እንደ ስድብና ኩነኔ የምንቆጥረው ለምን ሆነና? “ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡ አጭበርባሪና ስግብግብ ነጋዴዎች” የሚለው የአገራችን የተለመደ አባባል የዚህ ዝንባሌ መለያ ታፔላ ነው። “የሃብት ልዩነት ሰፍቷል” የሚለው ውግዘትም እንዲሁ።
መንግስት፤ የሙያና የቢዝነስ ሰዎች፣ በየመስኩ ፋብሪካ እየከፈቱ የኢንዱስትሪ ምርትን እንዲያስፋፉ ይመኛል። ምኞቱ እውን ሊሆን የሚችለው፤ የቢዝነስ ሰዎች ስኬታማና ትርፋማ ሲሆኑ ነው። ነገር ግን፤ የቢዝነስ ሰዎች ከሌላው ሰው የበለጠ ሃብት ማፍራታቸው መንግስትን አያስደስትም። “የሃብት ልዩነት”ን በደስታ ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለም። በደስታ ይቅርና፤ በዝምታ ወይም በቅሬታ ለመቀበልም አይፈልግም። “ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል” የሚለው ነገር አለ።
በፖለቲከኞቹ ቋንቋ “ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል” ማለት፤ ከታታሪ የፈጠራ ሰው (ማለትም ከስኬታማና ከትርፋማ ሰው) ሃብት በመውሰድ፤ ሃብትን በኪሳራ ለሚያባክንና ሃብትን ለማያፈራ ሰው መስጠት ማለት ነው። “ፍትሃዊ” ማለት፤ ሁሉንም ሰው እኩል ለማድረግ ፈጣን ሯጮችን ማንቋሸሽ፤ ቀን ከሌት ሲሰሩም፤ “አሸናፊ ለመሆን የሚመኙ በስግብግቦች” እያልን መወንጀል፤ ስኬታማዎች ወደ ፊት እንዳይራመዱ ቅልጥማቸውን ሰብሮ ማሳረፍ፣ ፈጣን ሯጭ ያልሆነውም ሰው እንዳይጣጣር ማባበል እንደማለት ነው።
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከመንግስት የተለየ አስተሳሰብ የለውም። ብቃትንና ስኬትን ከምር የሚፈልጉ ሰዎች፤ በብቃት የላቀ ስኬታማ ሰው ሲያጋጥማቸው በአድናቆትና በክብር ያሞግሱታል፤ በአርአያነቱም መንፈሳቸውን ያነቃቃሉ። ብዙ የአገሬ ሰዎች ግን፣ ቀልባቸው የሚማረከው አቅመቢስና “አለም በቃኝ” ብሎ ራሱን የጣለ ምስኪን ሲያጋጥማቸው ነው። ትርፋማነትንና ብልፅግናን የሚፈልጉ ሰዎች፤ ሃብትን በማፍራት የበለፀገ ትርፋማ የቢዝነስ ሰው ሲያጋጥማቸው፤ ውስጣቸው በአድናቆት ይሞላል፤ ታሪኩን ለማወቅ ይጓጓሉ። አብዛኛው የአገሬ ሰው ግን፤ የቢዝነስ ኩባንያን ሳይሆን የእርዳታ ድርጅትን፣ ለትርፍ የተቋቋመ ፋብሪካን ሳይሆን በበጎ አድራጎት የተተከለ ችግኝን በማስበለጥ እንደ ቅዱስ ነገር ያያል።
በአጭሩ፤ በነባር ተራ ቃላት፣ በተድበሰበሱ ምሁራዊ ሃረጋት ወይም በተሰለቹ ፖለቲካዊ አባባሎች ልዩ ልዩ ቀለም ብንቀባውም፤ አብዛኛው የዘመናችን አስተሳሰብ ከጥንታዊው የኋላቀርነት ባህል ብዙም አይለይም። “የዚህ አለም እውቀትና ሙያ እንደ ብናኝ ክብደት የሌለው፤ የዚህ አለም ደስታ እንደ ጤዛ ውሎ የማያድር፤ የዚህ አለም ስኬትና ብልፅግና እንደ ሸክላ ተሰባሪ፤ የዚህ አለም ኑሮና ምቾት እንደ ቅጠል ረጋፊ” … ከሚል የውድቀት ቅኝት አልተላቀቅንም። ራሳችንን ጠልፈን የመጣል አባዜ የተጠናወተንም በዚህ ምክንያት ነው። ይህንን ካስወገድን፤ የብቃትና የስኬት፣ የሥራ ፈጠራና የትርፋማነት፣ የሃብት ፈጠራና የብልፅግና ጉዟችንን የሚያሰናክል ከአቅም በላይ የሆነ እንቅፋት አይኖርብንም። ለነገሩ ብዙም ሊያከራክረን አይገባም ነበር፡፡ ምፅዋት የሚኖረው እኮ፣ በቅድሚያ የሃብት ፈጠራ ሲኖር ነው፡፡

Posted in politics | Leave a comment

ኢህአዴግ ሰራዊቱን በከፍተኛ ቁጥር ወደ ሰሜን እያጓጓዘ ነው

ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የደህንነት አባላት በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ፣ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሰራዊቱን አባላትና ከባድ
መሳሪያዎችን በምሽት ወደ ሽሬ፣ ተከዜ፣ ወልቃይት፣ መተማ፣ አርማጭሆ በመሳሰሉት የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እያጓጓዘ ነው።

ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ጋር በተያያዘ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የታው የህዝብ ቁጣ ያስደነገጠው መንግስት፣ ማንኛውም አይነት ተቃውሞ ቢነሳ በሚል ሰራዊቱንና ደህንነቱን እያሰማራ ነው።
ከሰሜን አካባቢዎች የመጡ የደህንነት አባላት፣ ግንቦት7 ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር ለአርሶ አደሩ የጦር መሳሪያ በማደል እስከ መሃል አገር ሊገባ ይችላል የሚል አስተያየት መስጠታቸውን
ተከትሎ ፣ ግንባሩ በድንበር አካባቢዎች ላሰማራቸው የድርጅቱ አባላት ባለሀብቶች ዘመናዊ ስልኮችን በማደል የስለላ ስራ እንዲሰሩ እንዳሰማራቸው ታውቋል።

ከተለያዩ የሰራዊቱ ክፍሎች የሚከዱ ወታደሮች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ ኢህአዴግ የሚጠፉ ወታደሮችን ለመተካት በሚል ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ
የተፈለገውን ያክል የሰው ሃይል አላስገኘለትም።

የኢህአዴግ ሰራዊት በከፍተኛ የሞራል ውድቀት ላይ መሆኑን የሚናገሩት ከሰራዊቱ የሚከዱ ወታደሮች፣ በዘር ላይ የተመሰረተው አደረጃጃት፣ የምግብ አቅርቦት መበላሸት እና የሰራዊቱ የኑሮ ሁኔታ ማሽቆልቆል
ለሰራዊቱ ሞራል መውደቅ ዋና ምክንያቶች ሆነው ይጠቀሳሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢህአዴግየመከፋፈልአደጋእንዳንዣበበት ምንጮች ገልጸዋል የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር በተለይ ከአቶ መለስ ሞት በኃላ አገሪትዋን መምራት ካለመቻሉ ጋርተ ያይዞ በዜጎች ላይየሚወስደው የጅምላ እስርና የማሳደድ ዘመቻ በራሱ አባላት ጭምር ጥያቄ እያስነሳ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ፓርቲዎች በሽብርተኛነት ሰም ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞች ላይ ያነጣጠረ የእስር እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉ በተለይ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራሩ አካባቢ ተቃውሞናጉ ምጉምታ እየተሰማ ነው፡፡
ምንጮች እንደገለጹት በኢህአዴ ግበኩል የሚወሰደውኢ-ዴሞክራሲያዊ እርምጃ የህዝብ አመኔታ
በማሳጣት የግንባሩን ሕልውና ችግር ላይ ይጥላል የሚሉ እና እየተወሰደያለውንጉልበትየታከለበትእርምጃ
በሚደግፉ አባላትና ከፍተኛ ካድሬዎች መካከል መቃቃር እየተፈጠረ መሆኑታውቋል፡፡

ግንባሩ በተፈጥሮው ከግምገማ በዘለለ የውስጥ ቅራኔን የሚፈታበት መንገድ የሌለው መሆኑና ልዩነቶች ከባድ ዋጋ የሚያስከፍሉ በመሆናቸው ምክንያት ቅሬታዎቹ ታምቀው እስካሁን መቆየታቸውን የገለጹት ምንጮቻችን በተለይ በሠላማዊ መንገድቅሬታውን ከሁለት ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ እየገለጸ ያለውን ሰ ፊየሙስሊም ማህበረሰብየተቃውሞድምጽለማፈንኃይልየታከለበትተደጋጋሚእርምጃ በረመዳን የጾም ወር መወሰዱ ሙስሊም የግንባሩን አባላት ጨምሮ በበርካታ አባላት ዘንድ ተቃውሞ እንዲቀጣጠል ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡

ኢህአዴግ በአሁኑ ወቅት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከጋዜጠኞች ፣ከሲቪል ማህበረሰብአባላት፣ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ፣ በብዛት ወጣቶችን ካቀፈው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማህበረ ቅዱሳን እንዲሁም
በኑሮ ውድነት ከሚሰቃየው ሰፊህብረተሰብ እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመላተሙ በመጪው ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሊመረጥ እንደማይችል መገንዘቡን ያስታወሱት ምንጮቹ በዚህ የተነሳ የትኛውንም ዓይነት ተቃውሞ በኃይል ለመደፍጠጥ ወስኖ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ይህየግንባሩ እርምጃ ትክክል አይደለም የሚሉ አባላት ብቅ ብቅ ማለታቸው ግንባሩ በቀጣይ ከባድ የመሰነጣጠቅ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል የመጀመሪያው ምልክት መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

Posted in politics | Leave a comment

ጅምላ ጨራሽ ተውሳክ (Biological Weapons) በድብቅ ወደ ትግራይ ተወሰደ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በመሰረቱ ጅምላ ጨራሽ ተውሳክ ወይም ባዮሎጂካል መርዝ በሰው ልጅ ላይ መጠቀም በተባበሩት መንግስታት የተከለከለ ነው። ሆኖም ይህንን የሰውን ልጅ በጅምላ የሚጨርስ ተውሳክ በህወሃት ጄነራሎች የሚመራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር በድብቅ ወደ አገር ውስጥ አስገብቶ ነበር። “ለምን እና በማን ላይ ግድያውን ለመፈጸም ነው?” የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ፤ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ክፍልም ቢሆን እንደዚህ አይነት ጥቆማ ቢደርሰው እርምጃ ለመውሰድ ይችላልና ኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶችን ይህንን ጉዳይ ልብ ሊሉት ይገባል። እናም ዛሬ የደረሰን ዘገባ እንዳመለከተው ከሆነ፤የዛሬ ዓመት በድብቅ ተጭነው ወደ አገር ቤት ውስጥ የገቡትን አንትራክስ ስፓርስ (anthrax spores )፥ ብሩሲሎሲስ (brucellosis)፣ እና ቦቱሊስም (botulism) የሚባሉ ጅምላ ጨራሽ ባዮሎጂካል መርዞች ታሽገው ከተቀመጡበት ደብረዘይት መከላከያ ኮሌጅ ላቦራቶሪ ውስጥ ወደ መቀሌ ዛሬ ሌሊት በኮንቴነር ተጭነው እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።

ጥቆማውን ያቀረበው እና አባ ኮስትር በሚል ስም መጠራት የመረጠው ግለሰብ ከሙያውም አንጻር ይህንን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ለግንዛቤ እንዲሆን ከዚህ በታች ያለውን የግንዛቤ ጽሁፍ አዘጋጅቶ አቅርቧል።

ሥነህይወታዊ በሽታ አምጭ(Biological Ethiologic Agents ) ተዉሳክን እንደ ጦር መሳርያ (Biological Weapons )የሰዉ ልጅ መጠቀም የጀመረዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 400 አ.አ የጦር ቀስትን በሞቱ እንስሳ ፈሳሽ ደምና የደም ተዋጾች መዘፍዘፍና ባላንጣን በመዉጋት ፤የኩሬ መጠጥ ዉሀን በመበከል እንደተጀመረ ከጤና ነክ መረጃወች መረዳት ይቻላል።የምራባዊያን ታሪካዊ ድርሳናትም ይህንኑ ያረጋግጣሉ።

የቅርቦችን ክንዉን ሰናስታዉስ በአንደኛዉ የአለም ጦርነት ጀርመን አንትራክስ (Anthrax)የተባለዉን በባክቴርያ በሶስት መንገዶች የሚዛመት ራሱን አካባቢዉ ሁኔታጋር በቀላሉ ሊቋቋም የሚችል(Spore former) እና በአፈር ላይ እስከ ፵ አመታት በላይ መቆየት የሚችል በተለይም ሳር የሚግጡ የቤት እንሰሳን የሚያጥቃ እና ከነሱ ጋር በሚደረግ ንክኪ ማለትም ቆዳቸዉ ሲነካ :-
1. በብነት መልክ በአየር(Aerosols )
2. ሰዉነታችን ላይ ቀላል ጭረት ካለ በንክኪ (Cutaneous) እንዲሁም
3. ሰጋቸዉንበመመገብ (Gastrointestinal) ወደ ሰወች የሚተላለፍ ሲሆን በተመሳሳይም ይህንኑ አንትራክስ በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት በጃፓን በሚስጥር በእስረኞች ላይ ተሞክሮ እስከ ሶስት ሺህ የሚሆኑ ሰወች ሰለባ ሆነወል።አሜሪካም ጀርመን በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ባዮሎጂካል መሳሪያን የምትጠቀም ከሆነ ምላሽ የሚሆናትን ለህክምናም ሆነ ለመከላከል አዳጋች የሆነዉን ለስጋ ዉጤቶች መመረዝ መንስኤ የሆነዉን ቦቱሊዝም የሚያመጣ (clostridium botulinum bacteria)የተሰኘ ባክቴሪያ ማዘጋጀትዋ ይታወሳል።በተጨማሪም ኤራቅ፤ ብሪታንያ፤ራሽያ ቬትናም የመሳሰሉ ሀገሮች የባዮሎጂካል ጦር መሳርያን የሚጠቀሙ ሲሆን በዉጤታማነቱም ሆነ በአቅርቦት ከኒውክሌር የተሻለና እጅግ ርካሽ መሆኑንም የተለያዩ የዘርፉ ምርምሮች ያመላክታሉ።
በዚህም መሰረት አንድ ግራም ባዮሎጂካል ቶክሲን (ቦቶሊዝም)አስር ሚሊዮን ያህል ሰዎችን በአንዴ ይገላል።ለምሳሌ ይሄዉ በላቦራቶሪ የተጣራ የቦቶሊዝም ቶክሲን የሰዉን ልጅ መተንፈሻ ና ነርቭ በማጥቃት ከሚታወቀዉ ሳሪን ኬሚካል ጦር መሳርያ(sarin chemical weapon ) ይልቅ ሶስት ሚሊዮን ጊዜ እጅግ ሲበዛ መርዛማ(potent) ነዉ።ቦቱሊዝም ሳሪን ኬሚካል ከሚሸፍነዉ የቆዳ ስፋት አንጻርም አንድ ግራም ቦቱሊዝም የሚባለዉን አደገኛ ገዳይ ቶክሲን አስራ ስድስት እጥፍ ማለትም ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ያህል(3700) ስኩየር ካሬ ሜትር ቦታ ይሽፍናል።
ሌላ ጊዜ በሰፊዉ የምመለስበት ሆኖ ለጥፋት የተዘጋጀዉ አፍሪካዊ ናዚ ወያኔ እነዚህን በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ የተከለከሉ የባዮሎጂካል የጦር መሳሪያወች(Biological Weapons) አከማችቶ መገኘቱ እንደምታ ሊጤን ፤ ሊታወቅ ና መረጃዉ ተጣርቶ አለም አቅፍ ትኩርት ሊሰጠዉና ወንጀለኛዉ ትግራይ መራሹ የወንበዴ ቡድን እጅከፈጅ (Redhanded) ተይዘዉ ለፍርደ እንዲቀርቡ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።

Posted in politics | Leave a comment

ቀጭን ግን ጠንካራዋ ኢትዮጵዊ ወጣት – ወይንሸት ሞላ

ስትሯሯጥ ትመለከቷቷላችሁ፡፡ ሰልፉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ደግሞ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ወይም የፓርቲዋን ሰማያዊ አርማ ይዛ ፊት ለፊት፣ በድፍረት ተቃውሞዋን ስታሰማ በተደጋጋሚ እመለከታት ነበር፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፣ በፖለቲካ ጉዳይ ላይ በድፍረት ከሰዎች ጋር የራሷ ሀሳቧ አንስታ ስትከራከር አይቻት አውቃለሁ፡፡ ተከራክራም የምትቀበለውን ‹‹ተስማምቻለሁ›› ስትል፣ እንዲሁም ባላሳመናት ነገር እና ሀሳብ ላይ የራሷ አቋም በመያዝ በልዩነት ክርክሯን ስታቆምም በሁለት አጋጣሚዎች ላይ ተመልክቻታለሁ፡፡
በሀገራችን፣ ብዙ እንስቶቻችን በፍርሃት ወጥመድ ሥር ወድቀው፣ በጣም ልስልስ የሆነ የህይወትን መስመርን ምርጫቸው አድርገውና ‹‹ፖለቲካን በሩቁ!›› በሚል መሪ ቃል የዘወትር ድግግሞሻዊ ሕይወት ውስጥ በምርጫ እየተጓዙ ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ፣ እንደወይንሸት አይነት ጥቂቶችን በፖለቲካ ዓለም ውስጥ ስመለከት እንደኢትዮጵዊ ዜጋ ደስታን ይፈጥርብኝ ነበር፡፡
…እንግዲህ ወጣቷ ወይኒ፣ ትናንት በአንዋር መስኪድ አከባቢ በተፈጠረው ረብሻ በፖሲሶች ተይዛ ከባድ ድብደባ እንደተፈጸመባት፣ ጭንቅላቷ በድብደባ ተጎድቶ እንደተሰፋና የቀኝ እጇ እንደተሰበረ ማኅበራዊ ድረ-ገጽ ላይ በተደጋጋሚ ከተጻፉ ጽሁፎች አንብቤ ተረድቻለሁ፡፡
የቆንጆ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የሆነችው እህቷ መልካም ሞላ፣ የማዕከላዊ አስር ቤት ጥዋት በስንት ሰዓት ለጥየቃ ክፍት እንደሚሆን ለማወቅ ጥዋት ደውላልኝ ነበር፡፡ ሰዓቱን ከነገርኳት ከሰዓታት በኋላ ስደውልላት እህቷ የታሰረችበትን ቦታ ጠይቃ እንዳወቀች እና ፍርድ ቤትም ልትቀርብ መሆኑን ነግራኝ ነበር፡፡ ወይንሸት ፍርድ ቤት ብትቀርብም እስከአሁን ማንም እንዳይጎበኛት ተከልክሏል – ባለኝ መረጃ መሰረት፡፡
በአሁን ሰዓት ማለት የምችለው አንድ ነገር ብቻ ሆነ!
ወይኒ፣ ፈጣሪ መንፈስሽን እና አካልሽን ይጠግነው! ዓምላክ ካንቺ እና ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር ይሁን!
አንድ አድርገን መልሰህ!

Posted in politics | Leave a comment